የዜጎች ቻርተር

መግቢያ

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የንግድና ገበያ ልማት  ቢሮ የክልሉ ም/ቤት የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 178/2011 መሠረት በአዲስ መልክ ሲደራጅ የንግድ አሰራር ስርአታችንን፣ በማጠናከር በተለይ ለግብርና ምርቶች በተለይም ኤክስፖርት ለሚደረጉ ምርቶች ገበያ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው በመሆኑ ይህን ሊሸከም የሚችል እና ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚችል አደረጃጀት በመለየት የተገልጋዩን ፍላጎት ማርካት በማስፈለጉ በስሩ የተለያዩ የዳይሬክቶሬቶችና ተጠሪ ተቋማትን አካትቶ ለዜጎች አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ ሆኖ ለዜጎች የሚሰጡ  ዋና ዋና አገልግሎቶች፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ /ስታንዳርድ/፣ የሚሰጡ አገልግሎቶች ቅድመ ሁኔታ፣ የቅሬታ አቀራረብና የግንኙነት ስርዓት ያካተተ ሥርዓት የመዘርጋት  ስልጣን ያለው መንግስታዊ ተቋም  ሲሆን፣ ቢሮም የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት አደረጃጀቶችንና የአሰራር ስርዓት ዘርግቶ ለዜጎች ተገቢውን አገልግሎት የማቅረብና መልካም አስተዳደር የማስፈን ግዴታና  ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ፣እና ፈጣን፣ ተደራሽና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ማግኘት የዜጎች  መብት በመሆኑ እና የአገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ለማሳለጥና ውጤታማነትን ለማረጋገጥ የተነደፈው መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ የተጠናው የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ (standard) መሠረት ዜጎች በላቀ ደረጃ የልማትና መልካም አስተዳደር ውጤት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከተጠቃሚዎች ጋር የአገልግሎት አሰጣጥ ውል በመግባት በሚሠጠው አገልግሎት የተገልጋዮችን እርካታ ማሳደግ አስፈላጊ ነው፡፡

በመሆኑም የደቡብ ብሔሮች ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ለዜጎች የሚሰጠውን አገልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር የሕዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ይህ የዜጎች የአገልግሎት አሰጣጥ ቻርተር ተዘጋጅቷል፡፡

  1. የቻርተሩ ዓላማ

የዚህ ቻርተር ዓላማ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሚሰጠውን አገልግሎት ለተገልጋዮች ግልጽ በማድረግ አገልግሎት የሚያገኙበት፣ ቅሬታ የሚያቀርቡበትና ምላሽ የሚሰጥበት የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ፣ ተደራሽና ጥራቱን የጠበቀ በማድረግ... ...Read more