የገበያ ልማትና ግብይት አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት

የገበያ ልማትና ግብይት አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት የሚያከናዉናቸዉ ዋና ተግባራት
 1. ነባር የገበያ ማዕከላትን ማጠናከርና ደረጃ በማውጣት የግብይቱን ሂደት ጤናማ እንዲሆን ማድረግ፤  
 2. የገበያ ማዕከላትን በተገቢው ቦታ ማደራጀትና ደረጃቸውን የጠበቁ በማድረግ ህጋዊ የሆነ ነጋዴ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ.፤ 
 3.  ዘመናዊ የግብይት ስርአት የማስፈን፣ የአሰራር ስርዓትን የመዘርጋት፣ ስራ  
 4. አዲስ  የሚገነቡ የገበያ ማዕከላትን በሌላ አካል እንዲገነቡ ማድረግና አፈጻጸሙን ስራ ሂደቱ እንዲከታተለው ማድረግ፤ 
 5. ለንግዱ ማህበረሰብ በዘመናዊ የግብይት ስርአት ላይ ስልጠና መስጠት፤  
 6. የዘርፍ ማህበራት፣የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትናየንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶችን ነባሮችን ማጠናከር፣ አዳዲሶችን ማደራጀትና ህጋዊ የምስክር ወረቀት መስጠት፤  
 7. የባዛርና ኤግዚቢሽን የማዘጋጀት ፈቃድ መስጠት፤መከታተልና ማጠናከር  
 8. ባዛርና ኤግዚቢሽን እንዲዘጋጅ ማድረግና ማዘጋጀት፤ማበረታታት፤ 
 9. የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶች ዋጋ መረጃ መተንተን  
 10. የገበያ ልማት ስራዎችን ውጤታማ የሚያደርጉ ጥናቶች ማካሄድና ስልጠና መስጠት፤  
 11. ዘመናዊ የግብይት እንቅስቃሴ በወሳኝነት እውን ማድረግ የሚቻለው የህብረተሰቡ ግንዛቤ አድጎ የግብይት እንቅስቃሴው ጤናማ እንዲሆን በሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ላይ ሙሉ ተሳትፎ ሲያደርግ ስለሆነ የግንዛቤ መፍጠርና ተሳትፎ የማሳደግ ተግባራት በሥራ ሂደት እንዲከናወኑ ማድረግ፤  
 12. የሥራ ሂደቱን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሳለጥና ህገ-ወጥነትን ለመከላከል በተደራጀ መንገድ የአጋር አካላትን ግንዛቤና ተሳትፎ ማሣደግ፣  
 13. ፍትሃዊና ህጋዊ የንግድ አሰራርን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት የመንግሥትና የግል ባለሃብቱን ትብብርና የጋራ ተሳትፎን ለማጠናከር የመንግሥትና የግል ባለሃብት የአጋርነት ፎረም/PPP/ ማቋቋም፣  
 14. የግብይት ስርኣቱ በህገወጥ ነጋዴዎችና ደላሎች ተጽእኖ ስር እንዳይወድቅ መከላከልና ሸማቹን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ፤  
 15. ህጋዊና የተጠናከረ የንግድ ዘርፍ ማህበራት ለማደራጀት የሚያስችል ግልጽ የሆነ የህግ ማእቀፍ ማዘጋጀትና ተግባራዊ ማድረግ፤   
 16. የዘልማድ ገበያዎችን በማጥናትና መሰረታዊ ልማቶችን እንዲሟሉ በማድረግ ደረጃቸውን ማሻሻል፤  
 17. በየደረጃው የአቅም ግንባታ ስራዎች መከናወን (Capacity building) ፤  
 18. ንግድ ነክ መመሪያዎችንና ማዋሎችን ማዘጋጀትና ማስተዋወቅ፤ማስፈጸም  
 19. ለገበያ በስፋት የሚፈለጉ  ምርቶች ፖቴንሻል አካባቢዎችን በጥናት በመለየት የማስተዋወቅና  በልዩ ልዩ ሚዲያዎች በመጠቀም ለህብረተሰቡ ማሳወቅ  
 20. ነባር የገበያ ማእከላትን  ለተጠቃሚው ተደራሽ አገልግሎት መስጠት በሚችሉበት አደረጃጀት መልሶ ማደራጀት፣  
 21. የአካባቢ ጥበቃን በዚህ ስራ ሂደት ሜይንስትሪም ማድረግ፣  
 22. ለንግዱ ማህበረሰብ የንግድ ስራ አመራራ ስልጠና በመስጠት የሚደግፉበትን አሰራር መዘርጋት፣  
 23. ከባለድርሻ አካላት ቋሚ  ምክክር መድረኮችን  የተቀናጀ የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት የስራ ሂደቱን ተግባራት  አሳታፊና ግልጽ በሆነ መንገድ መተግበር፣  
 24. የሥራ ሂደቱን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሳለጥና ህገ-ወጥነትን ለመከላከል ብሎም በተደራጀ መንገድ የአጋር አካላትን ግንዛቤና ተሳትፎ ማሣደግ የሚያስች የተመረጡና ተስማሚ የሆኑ የፕሮሞሽን ዘዴዎችን (Promotional Tools) መጠቀም፣  
 25. በግብይት ሥርዓቱ የሴቶችንና የወጣቶችን ተሳትፎ በማሳደግ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ፣