የሸማቾች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

የሸማቾች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መልክት

በንግድ ዉድድርና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ 813/2006 ሸማቾች ለደህንነታቸውና ለጤናቸው ተስማሚ የሆኑና ላወጡት ዋጋ ተመጣጣኝ የንግድ እቃዎችና አገልግሎቶች ማግኘት የሚችሉበት ሁኔታ ማመቻቸት እንደሚገባ ተደንግጓል፡፡ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ከህዝብ ክንፉና ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት አማራጭ የሌለዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ በመሆኑም ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ አካላት የሸማች መብት ማስከበር በየአካባዉ የሚታዬ የመልካም አስተዳደር ችግር መፍታት መሆኑን በመገንዘብ ሀላፊነታቸዉን እንዲወጡ መልክቴን አስተላፋለዉ፡፡

                                      በሸማቾች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሚሰሩ ስራዎች

               1.  የትምህርት፣የስልጠናና የድጋፍ ስራዎች፣
 • የሸማቾችን ግንዛቤ ለማዳበርና መብቱን ለማስከበር የሚያስችለውን ትምህርትና ሥልጠና መስጠት፣
 • ነጋዴዎች ለሸማቹ በህግ የተሰጡ መብቶችን እንዲያከብሩና የራሳቸውን ግዴታ መወጣት እንዲችሉ ማሰልጠን፣
 • አዋጆችን ደንቦችንና መመሪያዎችን ለሸማቾች፤ለነጋዴዎች እና ለባለድርሻ አካላት ማሰልጠን፣
 • ለሸማቾች የህብረት ስራ ማህበራት በሸማቾች መብት ላይ ስልጠና መስጠት፣
 • የሸማቾችን ተሳትፎ የማሳደግ ስራዎች፣
 • የሸማቹን ህብረተሰብ የመደራደርና ለመብቱ የመቆም አቅም የማሳደግ ስራዎች፣
 • የሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራትን አቅም የመገንባት፣ የመደገፍና የገበያ ትስስር የማስተሳሰር ስራዎች፣
 • ለሸማቾች መብት ጥበቃ ማህበር ድጋፍ የመስጠት ስራዎች፣
 • የሸማቾች ጥበቃና ድጋፍ ስራዎች ላይ የጥናት ስራዎችን መስራት፣
 • የኮሚኒኬሽን ስራዎች፣
              2. የምክርና የህግ ድጋፍ ስራዎች፣
 • የሸማቹን ቅሬታዎች መቀበል የሚቻልበትን ግልጽ ስርዓት መዘርጋትና ቅሬታውን በመቀበል ድጋፍ ማድረግ፣
 • ሸማቹ የደረሰበትን በደል ወደ ዳኝነት አካል አቅርቦ አስተዳደራዊና ፍትሃ-ብሄራዊ እርምጃዎች እንዲወሰድ ምክርና ድጋፍ መስጠት፣
 • ሸማቹ ህጋዊ መብቱን ለማስከበር ለፍርድ ቤቶች አቤቱታ ክስ ማቅረብ እንዲችል ተገቢውን የህግ ምክር ድጋፍ ማድረግ፣
 • ሸማቹ ለዳኝነት አካልና ለፍርድ ቤቶች ያቀረባቸው አቤቱታዎችና ክስ አፈጻጸም መከታተልና ለሸማቹ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ
            3.  የሸማቾችን መብትና ጥቅም የማስጠበቅ ሥራዎች፣
 • ሸማቹ ስለሚገዛው ዕቃ ወይም አገልግሎት ጥራትና አይነት በቂና ትክክለኛ መረጃ /መግለጫ / ስለማግኘቱ መከታተልና ማረጋገጥ፣
 • ሸማቹ ህብረተሰብ ከነጋዴው ለገዛው ዕቃ የተሰጠውን ዋስትና ማግኘቱን መከታተልና ማረጋገጥ፣
 • ሸማቹ የዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን ጥራት ወይም አማራጮችን በማየት የዋጋ ድርድር በማድረጉ ምክንያት እንዲገዛ አለመገደዱን መከታተልና ማረጋገጥ፣
 • በንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ግብይት ምክንያት ለሚደርስበት ጉዳት መካሱን ማረጋገጥና መከታተል፣
 • ማንኛውም ነጋዴ ስለሚሸጣቸው የንግድ ዕቃዎችና ስለሚሰጠው አገልግሎት ዋጋ መግለጫ ስለመለጠፉ መከታተልና ማረጋገጥ፣
 • በንግድ ዕቃዎች ላይ የሚለጠፉ መግለጫዎች አስፈላጊውን መረጃ ያሟሉና ግልጽ መሆናቸውን መከታተልና ማረጋገጥ፣
 • የምርትና የአገልግሎት ዋጋ ዝርዝር በግልጽ በሚታይ ቦታ ስለመለጠፉና ስራ ላይ ስለመዋላቸው መከታተልና ማረጋገጥ፣
 • ማንኛውም ነጋዴ ለሸጠው ዕቃ ወይም አገልግሎት ለሸማቹ ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ መወጣቱን ቀሪ መያዙን መከታተልና ማረጋገጥ፣
 • ሸማቹ ህብረተሰብ ከንግድ ዕቃና ከአገልግሎት ጋር በተያያዘ የሚፈልገውን መረጃ ከነጋዴው መውሰድ ስለመቻሉ ማረጋገጥ፣
 • ስለንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች በማንኛውም መንገድ የሚገለጹና የሚወጡ የንግድ ማስታወቂያዎች ሀሰተኛ ወይም አሳሳች አለመሆናቸውን መከታተል ማረጋገጥ፣
 • በሸማችና በነጋዴዎች መካከል የሚደረጉ የዉል ግዴታዎች ሸማቹ በህግ ያሉትን መብቶች እንዳይጠቀም የሚከለክሉት ወይም ነጋዴው በአዋጅ የተጣለበት ግዴ የሚያስቀሩ መሆናቸውን መከታተል፣
 • በማንኛውም ሰው ወይም ነጋዴ የሚፈጸሙ ተገቢ ያልሆኑና አሳሳች ተግባራትን መከታተልና መከላከል፣
             4.  የመሰረታዊ ፍጆታ ዕቃዎች ስርጭትና የገበያ ዋጋ መረጃ ስራዎች፣
 • ለሸማቹ ህብረተሰብ በመንግስት ድጎማ የሚቀርቡ መሠረታዊ ሸቀጦች ስርጭት ፍትሃዊነት መከታተልና ማረጋገጥ፣
 • በገበያ ውስጥ ያሉ የመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ስርጭት ችግሮችን መለየትና የመፍትሔ አቅጣጫ ማስቀመጥ፣
 • የገበያ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ ማጠናቀር እና ማሰራጨት፣