ከማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ጋር ተያይዞ የማሽነሪ ተከላዎችና የርክክብ ስራዎች ጊዜውን ጠብቆ በፍጥነት እየሄዱ ነው

በማኑፋክቸሪነግ ኢንዱስትሪው ዘርፍ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት አገልግሎት አሰጣጥ አንፃር አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠት፣ የተገነቡ ሼዶችና የማሽነሪ ሊዝ በጊዜው ርክክብ አለመፈፀም፣ የማሽነሪዎች አቅርቦት ክፍያ ከተፈፀመ በኋላ ወቅታዊነቱን ያልጠበቀ ርክክብና አቅርቦት፣ ማህበራት በጥቃቅን ተደራጅተው ሲበቁ ብድር አግኝተው ቶሎ ወደ ስራ አለማስገባትና የማምረቻ ቦታዎች መሰረተ ልማት አቅርቦት የታዩ አንዳንድ ችግሮች ናቸው ብለዋል፡፡
ወ/ሮ ገነት መኩሪያ አክለውም በንግዱ ዘርፍ በአብዛኛው የሚታዩት የመልካም አስተዳደር የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮችም ሆኑ አስተሳሰቦች በንግድ ምዝገባና ፈቃድ እድሳት፣ ከመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ፍላጎትና ስርጭት ጋር እንዲሁም ከዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዋንኛዎቹ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
በአሁኑ ሰአት ከባለድርሻ አካላትና ከህዝብ ክንፍ ጋር ተቀናጅተን በመታገላችንና በመስራታችን በተወሰነ መልኩ መሻሻል ካሳየንባቸው አንዱ በንግዱ ዘርፍ የፍጆታዎች እቃ አቅርቦትና ስርጭትሂደት እና የንግድ ምዝገባና ፈቃድ እድሳት በዞኖችና በወረዳኔት ኦን ላይን ሲስተም በተወሰነ ደረጃ ለውጥ ማምጣት መቻሉንና ገልፀዋል፡፡
ወ/ሮ ገነት መኩሪያ ከማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ጋር ተያይዞ የማሽነሪ ተከላዎችና የርክክብ ስራዎች ጊዜውን ጠብቆ በፍጥነት እየሄዱ ነው ያሉበት ሁኔታ የተሻለ አፈፃፀም እንደታየና በቀጣይ አሁንም መሰራት ያለባቸው በተለይም ከማሳያና ከመሸጫ ሼዶች ግንባታና ርክክብ ጋር ተያይዞ ያሉ ስራዎች ትግልና ትኩረት ተሰጥቶአቸው እየተሰሩ ያሉ ጉዳዮች መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡