charter

የደ/ብ/ብ/ሕ/ ክልላዊ መንግስት የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የክልሉ ም/ቤት የአስፈጻሚ   አካላትን እንደገና ለማቋቋም ባወጣው አዋጅ ቁጥር 161/2008 አንቀጽ 17 መሠረት በስሩ የተለያዩ ተቋማትንና የስራ ሂደቶችን አካትቶ ለዜጎች አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ ሆኖ ለዜጎች የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ /ስታንዳርድ/ ፣ የሚሰጡ አገልግሎቶች ቅድመ ሁኔታ፣ የቅሬታ አቀራረብና የግንኙነት ስርዓት ያካተተ ቻርተር የማዘጋጀት ስልጣን ያለው መንግስታዊ ተቋም  በመሆኑ፣  
ቢሮው የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት አደረጃጀቶችንና የአሰራር ስርዓት ዘርግቶ ለዜጎች ተገቢውን አገልግሎት የማቅረብ ግዴታና ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ፣
ፈጣን፣ ተደራሽና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ማግኘት የዜጎች መብት በመሆኑ፣
የአገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ለማሳለጥ መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ተጠንቶ ወደ ተግባር በተገባው መነሻ የተመዘገበውን ለውጥና መሻሻል በማስቀጠል ዜጎች በላቀ ደረጃ የልማትና መልካም አስተዳደር ውጤት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከተጠቃሚዎች ጋር የአገልግሎት አሰጣጥ ውል በመግባት አገልግሎቱን ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ፣
የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ለዜጎች የሚሰጠውን አገልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር የሕዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ይህ የዜጎች የአገልግሎት አሰጣጥ ቻርተር ተዘጋጅቷል፡፡