ዕቅድ

አገራችን ባለፉት አስርት ዓመታት ተከታታይነት ያለውን ባለሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘገበች ሲሆን ክልላችንም በተመሳሳይ ሁኔታ የመጀመሪያ ዙር ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ነድፎ ከአጠቃላይ ምርት በአማካይ 10.8 በመቶ ዕድገት በማሳየቱ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ዕድገት ተመዝግቧል፡፡ ከዚህ አንጻር በክልሉ ፈጣንና ቀጣይነት ያለውን ልማት ለማረጋገጥ ፤ ድኅነትን ለመቀነስና የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል በተለይም በከተሞች አካባቢ ሥር ሰዶ የቆየውን ሥራ አጥነትን ለማስወገድ በተቀመጠው ራዕይ መሰረት በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት እና በተለያዩ ዘርፎች በተደረገው ሁሉ አቀፍ ድጋፍ ሰፊ የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡
በመሆኑም የንግድና ኢንዱስትሪ ሴክተር ልማታዊ መልካም አስተዳደር ግቦች ዘርፉ የሚገኝበትን ነባራዊ ሁኔታና የአፈጻጸም ደረጃ በትክክለኛ አኳኋን ማመላከት እንዲችሉ አፈፃፀሞችን በመገምገም ዕቅዱን ማዘጋጀት ተገቢ ሆኖ ስለተገኘ የሁለተኛው ዙር የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የሀገራዊና የክልሉን የቀጣይ ዕድገት አቅጣጫን ተከትሎ አገራችን በ2017 ዓ.ም መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች የመጀመሪያ ተረታ ለማሰለፍ ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡