እንኳን ለ2011ዓ.ም አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ፣ የደቡብ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ዘመኑ የፍቅር፣ የሰላም የመደመርና የአንድነት ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞቱን እየገለፀ፣

ቢሮው በሀገራችን ብሎም በክልላችን የተጀመረውን የመደመር ጉዞአችንን በማፋጠን ሀገራችን የመጀመሪያ ደረጃ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለማሰለፍ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ወሳኙን ድርሻ ይዞ እየሰራ ይገኛል፣

ይሁን እንጂ በፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባራት ላይ ትግል በማድረግ፣ በመልካም አስተዳደር እርካታን በማረጋገጥና የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችን በላቀ ደረጃ በማሳካት በየደረጃው የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አላማው አድርጎ እየሰራ ቢሆንም፣ የሚስተዋለውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ብርቱ ስራ የሚጠበቅ መሆኑን አውቆ ለመፍታት ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

የማምረቻ ኢንዱስትሪውን በማስፋፋት መዋቅራዊ ሽግግሩን በማፋጠን፣ ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የነጻ ገበያ መርህ የተከተለ ንግድና ግብይት በማስፋፋት፣ የአምራቹን፣ የሸማቹንና የንግዱን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ፣

ኢንዱስትሪው የመሪነት ሚና እንዲኖረው አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ለማስፋፋት ሁሉ አቀፍ ድጋፍ በማድረግ ለኢንዱስትሪው ልማት መሰረት ከመጣል አልፎ በኢኮኖሚው ላይ የበኩሉን ድረሻ እንዲወጣ እየሰራ ይገኛል፡፡

በክልሉ የማምረቻ ኢንዱስትሪና ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጥሩ ተቋማት ተስፋፍተው፣ የኤክሰፖርት ምርቶች በዓይነት በመጠንና በጥራት አድገው፣ በቀጣይ ዕድገት ላይ የተመሰረተና በዓለም ተወዳዳሪ የሆነ የንግድና ግብይት ዘርፍ ተፈጥሮ የማየት ራዕይን አንግቦ የመደመር ጉዞውን የማፋጠን ላይ መሆኑንም ያስገነዝባል፡፡

በድጋሚ እንኳን ለ2011 አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ፣

የደቡብ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ዘመኑ የፍቅር፣ የሰላም የመደመርና የአንድነት ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞቱን ይገልፃል፣