የደቡብ ክልል ን/ገ/ል/ቢሮ ም/ኃላፊ እና የንግድ አሰራርና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ
የሀገራችንን ልማትና ዕድገት ቀጣይነት በማረጋገጥ የበለፀገች ኢትዮጲያን ለመገንባት በምናደርገው የለውጥ ጉዞ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ሴክተር ፍትኃዊ ቀልጣፋና የዘመነ የንግድ አሰራር ስርዓት ለማስፈንና ህገ-ወጥ ንግድን ለመቅረፍ የድርሻውን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡
እንደሚታወቀው በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ወደ ብልፅግና ለምታደርገው ጉዞ መሰረት ለመጣል ዘርፈ-ብዙ የለውጥ እንቅስቃሴ እተደረገ ይገኛል፡፡ይህንን ሁለንተናዊ የለውጥ እንቅስቃሴ እና የሀገር ግንባታ ሂደት አጠናክሮ ለማስቀጠል የዜጎች ተሳትፎ ማጎልበት፣ የመንግስትና የግሉ ሴክተር አጋርነትን ማጠናከር፤አስተማማኝ ሰላም ማረጋገጥና ልማትን ማፋጠን ወሳኝ ይሆናል፡፡